Sale!

Zemenawit/ዘመናዊት

190.00 Br

READ THE DESCRIPTION BELOW FOR MORE!!

ዘመናዊት መጽሃፍ ለዘመናይ ኢትዮዽያዊ ሴት የተዘጋጀ ተፈጥሮአዊ የውበት መጽሃፍ ሲሆን በውስጡም የተለያዩ የፍራፍሬ ፣አትክልት ፣ጥራጥሬ እንዲሁም አንዳንድ የእንሣት ተዋጽኦ ውህዶች ይገኙበታል ። ዘመናዊት መጽሃፍ በማንኛውም እድሜ ላለች ሴት የሚሆን ሲሆን ፣ ተፈጥሮአዊ ውበትን ለመጠበቅ እና ለመንከባከብ የተዘጋጀ መጽሃፍ ነው ። ዘመናዊት መጽሃፍ በውስጡ ሰባት ምእራፎች ያሉት ሲሆን ፣ በመጽሃፉም ውስጥ ማንኛዋም ሴት የተፈጥሮ ውበትዋን ለመጠበቅ ልታውቀው የሚገባ የተለያዩ ሀሳቦችና ምክሮች እንዲሁም ሁሉም ሴቶች ሊያደርጓቸው የሚገቡ ቅድመ-ዝግጅቶች የያዘ ሲሆን በተጨማሪም ለፀጉር ፣ለፊት ፣ለሰውነት እንዲሁም ለእጅ እና እግር መንከባከቢያ የሚጠቅሙ የተፈጥሮ ውህዶችን በውስጡ አካቷል ፣ እንዲሁም ማንኛውንም የጸጉር ወይም የቆዳ መንከባከቢያ ምርቶችን ከመግዛት በፊት መደረግ ያለበትን ጥንቃቄ ያስረዳል ።

ዘመናዊት መጽሃፍን የግሎ በማድረግ በተፈጥሮ ወይም ሰው ሰራሽ ምክንያት የተጎዳውን የተፈጥሮ ውበትዎን ማከም ወይም መንከባከብ ያስችሎታል ። በዘመናዊት መጽሃፍ ውስጥ ያሉትን ውህዶች በመጠቀም ጸጉርን እንዲሁም ቆዳን ያማረ እና ጤናማ በማድረግ በራስ መተማመኖን በመጨመር ደስተኛ እና ቀላል ህይወት እንዲኖሮት ያደርጋል ። ዘመናዊት መጽሃፍን በማንበብ የተለያዩ ሰው ሰራሽ ምርቶችን ከመግዛት እና ከመጠቀም በፊት የተለያዩ ጎንዮሽ ጉዳት ያላቸውን ኬሚካሎችን ለመለየት እና እራስን ከተለያዪ በሽታዎች ለመከላከል መረጃ ለማግኘት ያስችላል ።

ጸሃፊ ቃልኪዳን ኪሩቤል

ቃልኪዳን ኪሩቤል በኢትዮዽያ አዲስ አበባ ተወልዳ ያደገች ሲሆን በአሁኑ ሰአት የሶስት ልጆች እናት ናት ። የኢትዮዽያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ በመሆን ለሶስት አመታት ያገለገለች ሲሆን በአሁኑ ሰአት IT(QA analyst) በመሆን በመስራት ላይ ትገኛለች ። ለተፈጥሮ ልዩ የሆነ ፍቅር ያላት ሲሆን እንደ ማንኛውም ሴት ውበትን መንከባካብ እና መጠበቅ ያስደስታታል ፣ ፍራፍሬዎችን እንዲሁም የተለያዩ ተፈጥሮአዊ ነገሮችን በመጠቀም ውባትን መጠበቅ ለብዙ አመታት ልምዱ ያላት ሲሆን በጣም ብዙ ውጤትም አግኝታበታለች ፣በዚህም ምክንያት ዘመናዊት የተሰኘውን የውበት መጽሃፍ ለማሳተምና ለኢትዮዽያውያን ሴት እህቶች ለማካፈል በቅታለች።

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “Zemenawit/ዘመናዊት”

Your email address will not be published. Required fields are marked *